ተደጋጋሚ ጥያቄዎችና መልሶች
ስለ ቺፕቺፕ፣ በጋራ ስለ መግዛትና ስለ ቀጣይ እርምጃዎች።
የቡድን ግዢ
በዚህ ድረ ገጽ ላይ ማዘዝ እችላለሁ?
ለጊዜው አይቻልም። ምርቶችን መምረጥና ማዘዝ የሚቻለው በመተግበሪያው ነው። ድርጅቶች መዳረሻ ለማግኘት ቡድናችንን ማነጋገር ይችላሉ፤ የማህበረሰብ ሸማቾች ደግሞ የሸማቾችን መተግበሪያ ይጠቀማሉ። የቺፕቺፕ መተግበሪያን ያውርዱ →
የሱፐር ሊደር ሚና ምንድን ነው?
ሱፐር ሊደሮች የማህበረሰብ አባላትን ያሰባስባሉ፤ ትዕዛዞችን ያጠቃልላሉ፤ የተስማሙበትን ርክክብም ያስተባብራሉ። ከመመዝገብዎ በፊት የተቀመጡትን መስፈርቶች ያንብቡ። የብቁነት መስፈርቶችና ምዝገባ →
Smart Souk ምንድን ነው?
ሰፋ ያሉ ማህበረሰቦችን፣ የተጠቃለሉ ትዕዛዞችንና ዕቃ መረከቢያዎችን ለማቀናጀት በዕድገት ላይ ያለ አቅጣጫችን ነው። Smart Souk በቡድን ግዢና በሱፐር ሊደሮች ላይ የሚገነባ ሲሆን፣ በአካባቢዎ መኖሩ መረጋገጥ አለበት። በአካባቢዎ ስለመኖሩ ይጠይቁ →
ለድርጅቶች የግዢ መተግበሪያ
ድርጅቴ የግድ ቡድን መቀላቀል አለበት?
አያስፈልግም። የንግድ መተግበሪያ መዳረሻ ካገኙ በኋላ፣ የሚገኙ ምርቶችን መርጠው ለድርጅትዎ ራስዎ ማዘዝ ይችላሉ። የማህበረሰብ ቡድን መቀላቀል አያስፈልግም። የንግድ መተግበሪያ መዳረሻ ይጠይቁ →
ድርጅቴ በመተግበሪያው ምን ማድረግ ይችላል?
ምርቶችን መመልከት፣ መምረጥና ማዘዝ ይችላሉ። ትዕዛዝዎ የደረሰበትን ደረጃና ቀላል የድርጅትዎን የፋይናንስ ሪፖርቶችም ማየት ይችላሉ። መዳረሻ ለማግኘት ቡድናችንን ያነጋግሩ። የንግድ መተግበሪያ መዳረሻ ይጠይቁ →
የክፍያ ጊዜ አማራጩ እንዴት ይሠራል?
ይህ አማራጭ ለተመረጡ የንግድ ደንበኞች ብቻ ይሰጣል። ከመፈቀዱ በፊት የድርጅቱ ብቁነት፣ የፋይናንስ ገደብና የመክፈያ ጊዜ በተናጠል ይገመገማሉ። ስለ ብቁነት ይጠይቁ →
አገልግሎቱ የትኞቹን ምርቶችና አካባቢዎች ያካትታል?
ድርጅቶች በመተግበሪያው የሚገኙ ምርቶችን መመልከት ይችላሉ። የምርትና የማድረስ አቅርቦት እንደ አካባቢዎ ይለያያል። ስለ አገልግሎት ክልል ወይም ምርት ስለማቅረብ ቡድናችንን ያነጋግሩ። በድረ ገጹ ጥያቄ ማቅረብ ትዕዛዝ መስጠት አይደለም። ከቡድናችን ጋር ይነጋገሩ →
አቅራቢዎች
እንዴት አቅራቢ መሆን እችላለሁ?
የአቅራቢነት ቅጹን ከፍተው የሚያቀርቧቸውን ምርቶች፣ አካባቢዎንና የመገናኛ መረጃዎን ያስገቡ። ቡድናችን ጥያቄዎን ይመለከታል። ቅጹን መሙላት የአቅራቢነት ፈቃድ አይደለም። የአቅራቢነት ቅጹን ይክፈቱ →
የደንበኞች ድጋፍ
ቀደም ሲል ስላዘዝኩት ትዕዛዝ ድጋፍ የት ማግኘት እችላለሁ?
በቺፕቺፕ መተግበሪያ ያለውን የእርዳታ ክፍል ይጠቀሙ፤ በ +251 111 139 770 ይደውሉ፤ ወይም ወደ support@chipchip.social ይጻፉ። እባክዎ የይለፍ ቃል ወይም የክፍያ መረጃዎችን ለማንም አያጋሩ። የደንበኞች ድጋፍን ያነጋግሩ →